የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ መልክት አስተላለፉ

በስመአብ ወወልድ ወመነፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡

ትውልድ ሆይ የእግዚአብሔር ቃል ተመልከቱ ሰው መንፈሳዊ ምግቡ የእግዚአብሔር ቃል ሁል ጊዜ መመገብ አለበት፣

የመላእክት ምግብ ቃለ እግዚአብሔር ነው ፡፡ት.ኤር. 2-31

እኛም ሰዎች ምንም እንኳ ምድራውያን ብንሆንም ሰማያዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እንመገባለን፡፡ ሰው ለግዜው የዚህ ዓለም ቁሳዊ የሆነውን ብያምሮውና ብያባብለው ሄዶ ሄዶ ገነት መንግስተ ሰማያት በሚገባበት ሰዓት ገነት መንግስተ ሰማያት ሲገባ የሚመገበው ሰማያዊ የሆነውን ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡

banner

ቃለ እግዚአብሔር የሚያዘወትር ሰው ወይም የእግዚአብሔር ፍቅር ያለው ሰው ሃይማኖትን ይጠብቃል፡፡ ሃይማኖትን ጠብቆ አፅንቶ ይኖራል፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያድርበታል፣ ፀጋ እግዚአብሔር ይበዛበታል፣ የሰው ፍቅር ይበዛለታል፣ የሃገሩና የሃይማኖቱ ቅርስና ታሪክ ይጠብቃል፣ ያስጠብቃል፣ እንዲህም ፀሎቶኛና ደግ ሰው ይሆናል፣ የቅዱሳን በረከት የድንግል ማርያም አማላጅነት ፍቅር ያበዛለታል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ፍፁም ንፁህ የጠራ ቃል ነውና እግዚአብሔር ለሙሴ ከወንድሞቻቸው መካከል እንደአንተ ያለ ነብዩ አስነስላችዋለሁ ቃሉንም በአፍ አደርጋለሁ፣ የአዘዝኩትንም ቃል ሁሉም ይነግራቸዋል፣ በስሜም የሚናገረውን ቃል የማይሰማውን ሰው እኔ እበቀልለታለው ብለዋል እግዚአብሔር በቃሉ ዘዳግም 18፡18 ስለዚህም በመጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው ሁሉም የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው፡፡ ቃለ እግዚአብሔር ለህይወታችን ገንቢና ጠቃሚ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ግዜ እንደሚነግረን ለቤተክርስትያናችን አስፈላጊ ነገሮች በማሟላት እንዲሁም በመንበረ ጽባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያለው የቅርስና የታሪክ ማዳረሻ ወይም የሀይማኖታችን ታሪክ መለያ መጥታችሁ እንድትጐበኙ መልእክታችን ነው፡፡ እንዲሁም የካቴድራሉ አቅም የሚደግፍና የሚያግዝ የኢኮኖሚ እድገት የሚያመጣ እየተሰራ ያለው ልማት ፕሮጀክት አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ሃይማኖታዊ ግዴታችሁ እንድትወጡ መልእክታችን ነው፡፡

የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ

ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ