“ዋዋጎ” ቱውፊታዊ ድራማ ተመርቆ ለምእመናን እይታ ክፍት ሆኗል፡፡

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እድሳት ገንዘብ ማሰባሰቢ ያሚሆን በሊቀጉበኤ ታረቀኝ ብርሃኑ ተደርሶ በመርሐዬ ተውኔት ጥላሁን ዘውገ እና በታዋቂ አርቲስቶች የተተወነ “ዋዋጎ” የተሰኘ መንፈሳዊ እና ቱውፊታዊ ቲያትር ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የበላይ ጠባቂ፣ የተለያዩ አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ማኅበረ ካህናት እና ምእመናን በተገኙበት ቅዳሜ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ/ም በቡራኬ ተመርቆ ለምእመናን እይታ ክፍት ሆኗል፡፡

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳደር እና ሰበካ ጉባኤው በቃለ አዋዲው ደንብና ሕግ መሠረት እራሱን የቻለ የሕንፃ ዕድሳት አሠሪ ዐቢይ ኮሚቴ በማዋቀር ልዩ ልዩ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ቆይቶ በቅርስ ጥገና ሥራ ላይ ሙያ ያላቸውን መሐንዲሶችን በማሳተፍ እንዲሁም በሀገሪቱ ካለው የቅርስ ጥበቃ ባለ ሥልጣን መ/ቤት ጋር ምክክር በማድረግ የካቴድራሉ ሕንፃ በከፍተኛ ደረጃ ዕድሳት እየተደረገለት ይገኛል፡፡ ለካቴድራሉ ዕድሳት ሙሉ ገቢ የሚሆን “ዋዋጎ” የተሰኘ የአብነት ትምህርት ቤቶች እና የቅኔ ትምህርት ቤቶች ለቤተክርስትያን ያላቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላይ ያጠነጠነ እንዲሁም የገጠሪቷን ቤተክርስትያን ችግር አጉልቶ የሚያሳይ ድንቅ መንፈሳዊ ድራማ ከአርቲስቶች ጋር በመተባበበር በመታየት ላይ ይገኛል፡፡ በትዕይንቱ እየተማሩ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራልን ሕንፃ እድሳት ይደግፉ፡፡

ቲያትሩ ቅዳሜ ሐምሌ 1 ፣ 15 እና 22 ቀን 2015 ዓ/ም በካቴድራሉ ሁለገብ አዳራሽ ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ ከተለያዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ጋር ይቀርብላችኃል፡፡ የመግቢያ ትኬቱን በዕለቱ የሚገኙ ሲሆን ዋጋውም 200.00ብር እና 300.00 ብር መሆኑንን አዘጋጅ ኮሚቴው ገልጸል፡፡