የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 6ኛውን የፓትሪያርክ ምርጫ የካቲት 21/2005 ዓ.ም እንደምታካሂድ አስታወቀች፡፡

                                በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

7

ድስተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ለማስመረጥ የተቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ ከምርጫው ሂደት ጋርና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ በተመለከተ ዛሬ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለጋዜጠኞች ወቅታዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዚሁም መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 6ኛ የፓትሪያሪክ ምርጫ ለማካሄድ ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው መሠረት ከሊቃነ ዻዻሳት ፣ከጠቅላይ ቤተክህነት ሰራተኞች ከአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ከሰንበት ትምህርት ቤቶች እና ከማህበረ ቅዱሳን የተውጣጣ 13 አባላት ያለው አሰመራጭ ኮሚቴ አቋቋማ ዝግጅት ሰታደረግ መቆየቷ ይታወቃል፡፡

በዚሁም መሠረት ኮሚቴው ምርጫው የሚካሄድበት ቀንና የምርጫውን ፕሮገራም በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል ፡፡ የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢና የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ ብፁዕ አቡነ እሰጢፋኖስ በመግለጫው እንዳሉት የመጨረሻውን ምርጫ የሚያከናውኑት ከሊቃነዻዻሳት፣ ከገዳማትና አድባራት፣ ከካህናት፣ ከምዕመናን፣ ከሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እና ከማሀበረ ቅዱሳን የተውጣጡ በአጠቃላይ 800 ሰዎቸ ናቸው ብለዋል፡፡

የምርጫውን ሂደት ለማስፈጸም የወጣው መግለጫ ምእመናን ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው ማንነታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ በመያዝ ለእጩነት የሚያስቡትን አባት አስመራጭ ኮሚቴው ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመቅረብ እንዲሁም ከሀገር ውጪ የሚገኙ በፋክስ ቁጥር 0111567711 እና 0111580540 ከየካቲት 1 እስከ 8 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲጠቁሙ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

አስመራጭ ኮሚቴው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ የካቲት18/2005 ዓ.ም አምስት እጩዎችን ይፋ ያደርጋል ፡፡ ምርጫውን ለማካሄድ ከ53 አህጉር ስብከት፣ ከካህናት፣ ከምዕመናን፣ ከሰንበት ተማሪዎች የተውጣጡ 13 አባላት ተመርጠው የካቲት 19 አዲስ አበባ እንደሚገቡም አስታውቀዋል፡፡

ምርጫው የሚካሄድበት ቀንም የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ምርጫው ተከናውኖ፣ በዚሁ ዕለት ምሽት 12 ሰዓት ላይ ውጤቱ ለሕዝቡ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቋል፡፡ ምርጫው የዓለም አብያተክርስቲያናት ማህበር፣ የአፍሪካ አብያተክርስቲያናት ምክር ቤት ተወካዮች እና ምዕመናን እንደሚታዘቡትም ገልፀዋል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ የወደደውንና የፈቀደውን ቤተ ክርስቲያንን የሚመራ አባት በመንበሩ ያስቀምጥ ዘንድ ካህናትና ምእመናን ከየካቲት 1 እስከ 8 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ አምላካቸውን በጸሎት እንዲጠይቁ ለአንድ ሱባኤ የሚቆይ የጸሎት ጊዜ መታወጁን አስታውቋል፡ የፓትርያርኩ በዐለ ሲመቱም እሁድ የካቲት 24/2005 ዓ.ም በመንበረ ጸበዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚካሄድም አስታውቀዋል፡፡