banner

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለካቴደራሉ እድሳት የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተካሄደ

በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

bannerቀደም ሲል የዘሁ ዓይነት መርሃ ግብር መጋቢት 10/2004 ዓ.ም ተካሂዶ የነበረ ሲሆን በድጋሚ በሳለፍነው ሳምንት ሰኔ 24/2004 ለሁለተኛ ጊዜ ተካሂዷል በዚሁ ዕለት እነ መሠረት መብራቴን ጨምሮ ታዋቂ አርቲስቶች የተገኙ ሲሆን ዕለቱን አስመልክቶ ያዘጋጁትን መዝሙር፣ ድራማና ግጥም ለታዳሚዎች ምእመናን አቅርበዋል አበረታች የሆነ ውጤትም ተገኝቷል በቀጣይም የዚህ ዓይነት መርሃ ግብር ሊዘጋጅ እንደሚችል የካቴድራሉ አስተዳደር ገልጿል፡፡banner

በሌላ ዜና የካቴድራሉ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ሰርቲፊኬት ሐምሌ 1/2004 ዓ.ም የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ በተገኙበት መርሃ ግብሩ ተካሂዷል፡፡ በዚሁ ዕለት ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎችና ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች በካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ ሽልማት ተሰጧቸዋል፡፡

ዓመታዊው የዓጋዓዝተ ዓለም ሥላሴ በዓል በድምቀት ተከበረ

በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚከበረው ዓመታዊው  የሥላሴ በዓል በዚህ ዓመትም በመንበረ ጸባዖት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኩሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንትና ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡፡

በዓሉ መከበር የጀመረው ከዋዜማው ከሐምሌ6 ጀምሮ ሲሆን የካቴድራሉ ካህናትና መዘምራን ከዋዜማው ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ለ24 ሰዓታት ያህል ሌሊትና ቀኑን ሙሉ ያለ ማቋረጥ ስብሃተ እግዚአብሔር ሲያቀርቡ ውለው አድረዋል፡፡

ይህመንፈሳዊ አገልግሎት ማለትም ስርዓተማህሌተ፣ ስርዓተቅዳሴ እንዲሁም ሰዓታትና ሰርክ ፀሎት በአጠቃለይ የስርዓተ አምልኮ አፈፃፀም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ልዩ በመሆኑ የእምነቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም እጀግ በጣም የሚስደንቅ በዓል ነው፡፡

በሌላ ዜና የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኩሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት 20ኛው በዓለ ሲመት ሐመሌ 5/11/04 ዓ.ም በካቴድራሉ በታላቅ ደምቀት ተከብሮ ውልዋል፡፡

 

በበዓሉ ላይ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ፣የመንግስት ተወካይ፣ የኦሬንታል ቤ/ክ ተወካዮች፣የአፍሪካ ቤ/ክ ዋናፀሐፊ የአ.አአ ዳባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ፀሐፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና እንዲሁም በብዙሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡

የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል 1ኛ እና 2ኛ ደረጅ ት/ቤት የክረምትና የ2005ዓ.ም መደበኛ ት/ት ምዝገባ ጀመረ

በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል 1ኛ እና 2ኛ ደረጅ ት/ቤት የክረምትና የ2005ዓ.ም መደበኛ ት/ት ምዝገባ ከዚህ ቀጥሎ ባለው መርሃ ግብር/እስከጁል መሠረት መሆኑን የካቴድራሉ ት/ቤት አስተዳደር ገልጿል

የመመዝገቢያ ጊዜ

የክፍል ደረጃ

የተመዝጋቢው ዓይነት

ክፍያ

ት/ት የሚሰጥበት ጊዜ

ለክረምት

ለመደበኛ

 

ለነባርና አዲስ የክረምት  ተማሪዎች

ከሐምሌ 2-7/2004

ኬጂ1-ኬጂ3

ነባር

150

 

ከሓምሌ9-ነሐሴ21/2005

1ኛ-4ኛ

››

120

170

5ኛ-6ኛ

››

140

190

7-8ኛ

››

150

200

9ኛ-10ኛ

››

250

320

11ኛ-12ኛ

››

250

395

 

ለአዲስ ተማሪዎች

ከሐምሌ 2-7/2004

1ኛ-4ኛ

አዲስ

120

170

ከመስከረም2-ሰኔ30/2005

5ኛ-6ኛ

››

140

190

7-8ኛ

››

150

200

9ኛ-10ኛ

››

300

320

11ኛ-12ኛ

››

300

395

ኬጂ1-ኬጂ3

››

150

 

 

ማሳሰቢያ፡- ለሁሉም ተማሪዎች መመዝገቢያ አይጨምርም

የመመዝገቢያ ጊዜ

የክፍል ደረጃ

የተመዝጋቢው ዓይነት

ክፍያ

ት/ት የሚሰጥበት ጊዜ

ለክረምት

ለመደበኛ

 

ለነባርና አዲስ የክረምት ተማሪዎች

ከሐምሌ 2-7/2004

ኬጂ1-ኬጂ3

ነባር

150

 

ከሓምሌ9-ነሐሴ21/2005

1ኛ-4ኛ

››

120

170

5ኛ-6ኛ

››

140

190

7-8ኛ

››

150

200

9ኛ-10ኛ

››

250

320

11ኛ-12ኛ

››

250

395

 

ለአዲስ ተማሪዎች

ከሐምሌ 15/2004 እስከ ነሐሴ 15/2004

1ኛ-4ኛ

አዲስ

120

170

ከመስከረም2-ሰኔ20/2005

5ኛ-6ኛ

››

140

190

7-8ኛ

››

150

200

9ኛ-10ኛ

››

300

320

11ኛ-12ኛ

››

300

395

ኬጂ1-ኬጂ3

››

150

 

banner

The Korean Ambassador’s visit the Holy Trinity Cathedral

በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

banner

The Ethio-south Korean relationship has a long history. It goes back to the 1950s. The Republic of Korea, after officially separated, from North Korea by the UN Resolution but the North Korean with the support of USSR, however needed to unify the two Koreans by force. This led to Korea war of 1950-1953. In the war, the communist Korea was assisted by USSR and China. The UN forces in which the Ethiopian Army was a major component supported the South. As the matter of interest, the Ethiopian contingent under the UN named as “Qagnew” regiment fought bravely on the side of The Republic of Korea and some of the solders sacrifice their life. Those patriots who had lost their life have rested here in The Holy Trinity Cathedral.

On June 3, 2012 the Republic of Korean Ambassador to Ethiopia Mr. Jong Geun Kim visited The Holy Trinity Cathedral where the patriots of the Korean war have rested. On his visit, the Ambassador was welcomed by his Excellency Leake Seltanat Abba Gebrselase Belay head of the Holy Trinity Cathedral and all staff members of the cathedral .Mr. Jong Geun Kim also donated 5,000 birr to the cathedral and promised to work with the cathedral in the future.

banner

የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ መልክት አስተላለፉ

በስመአብ ወወልድ ወመነፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡

ትውልድ ሆይ የእግዚአብሔር ቃል ተመልከቱ ሰው መንፈሳዊ ምግቡ የእግዚአብሔር ቃል ሁል ጊዜ መመገብ አለበት፣

የመላእክት ምግብ ቃለ እግዚአብሔር ነው ፡፡ት.ኤር. 2-31

እኛም ሰዎች ምንም እንኳ ምድራውያን ብንሆንም ሰማያዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እንመገባለን፡፡ ሰው ለግዜው የዚህ ዓለም ቁሳዊ የሆነውን ብያምሮውና ብያባብለው ሄዶ ሄዶ ገነት መንግስተ ሰማያት በሚገባበት ሰዓት ገነት መንግስተ ሰማያት ሲገባ የሚመገበው ሰማያዊ የሆነውን ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡

banner

ቃለ እግዚአብሔር የሚያዘወትር ሰው ወይም የእግዚአብሔር ፍቅር ያለው ሰው ሃይማኖትን ይጠብቃል፡፡ ሃይማኖትን ጠብቆ አፅንቶ ይኖራል፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያድርበታል፣ ፀጋ እግዚአብሔር ይበዛበታል፣ የሰው ፍቅር ይበዛለታል፣ የሃገሩና የሃይማኖቱ ቅርስና ታሪክ ይጠብቃል፣ ያስጠብቃል፣ እንዲህም ፀሎቶኛና ደግ ሰው ይሆናል፣ የቅዱሳን በረከት የድንግል ማርያም አማላጅነት ፍቅር ያበዛለታል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ፍፁም ንፁህ የጠራ ቃል ነውና እግዚአብሔር ለሙሴ ከወንድሞቻቸው መካከል እንደአንተ ያለ ነብዩ አስነስላችዋለሁ ቃሉንም በአፍ አደርጋለሁ፣ የአዘዝኩትንም ቃል ሁሉም ይነግራቸዋል፣ በስሜም የሚናገረውን ቃል የማይሰማውን ሰው እኔ እበቀልለታለው ብለዋል እግዚአብሔር በቃሉ ዘዳግም 18፡18 ስለዚህም በመጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው ሁሉም የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው፡፡ ቃለ እግዚአብሔር ለህይወታችን ገንቢና ጠቃሚ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ግዜ እንደሚነግረን ለቤተክርስትያናችን አስፈላጊ ነገሮች በማሟላት እንዲሁም በመንበረ ጽባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያለው የቅርስና የታሪክ ማዳረሻ ወይም የሀይማኖታችን ታሪክ መለያ መጥታችሁ እንድትጐበኙ መልእክታችን ነው፡፡ እንዲሁም የካቴድራሉ አቅም የሚደግፍና የሚያግዝ የኢኮኖሚ እድገት የሚያመጣ እየተሰራ ያለው ልማት ፕሮጀክት አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ሃይማኖታዊ ግዴታችሁ እንድትወጡ መልእክታችን ነው፡፡

የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ

ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ

አዲሱ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

 

በቅዱስነታቸው መልካም ፈቃድ አማካኝነት ከየካቲት 1 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም. ጀምሮ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ ሲሆኑ እሁድ የካቲት 4 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም. የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባዔ፣ ካህናት፣ መዘምራን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና የአጥቢየው ምእመናን ደማቅ አቀባበል አድርጐላቸዋል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የካቴድራሉ የበላይ ጠባቂና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ የቀድሞ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ የነበሩት ሊቀሊቃውንት አባ ጥዑመልሳን ኪ/ማርያም የአሁኑ የታዕካ ነገስት ባዕታ ለማርያም ገዳም አስተዳዳሪና ሌሎች የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችም ተገኝተዋል በዓሉን አስመልክቶም ከደብረ ገነት መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ሊቃውነት ቅኔ ቀርቧል፡፡ ዕለቱን አስመልክተው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ቤተክርስቲያን አንዲት ናት፣ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ አባቶቻችን ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወሩ ቤተክርስቲያንና ህዝበ ክርስቲያንን ይመራሉ፣ ያስተምራሉ፣ ለዚህም ነው ዛሬ ሁለቱም አባቶቻችን (ወንድሞቻችን) ከመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወደ ባዕታና ከደብረ ገነት መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አንዲቷን ቤተክርስቲያን ለማገልገልና ሐዋርያዊ ተልዕኮአቸውን ለመፈፀም የተዛወሩት ብለዋል፡፡

 

ምንም እንኳን የቦታው ስም ቢለያይም የቤተክርስቲያቱ አገልግሎት አንድ መሆኑን አበክረው ገልፀዋል፡፡ ከብፁዕ አቡነ አረጋዊ በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የቀድሞ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ የነበሩት ሊቀሊቃውንት አባ ጥዑመልሳን ኪ/ማርያም ሲሆኑ ለአዲሱ አስተዳዳሪ እንኳን ደህና መጡ በማለት ደስታቸውን ከገለፁ በኋላ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መላ ማህበረካህናትና ልዩ ልዩ ሠራተኞች በነበራቸው የስድስት ዓመታት ቆይታ እጅግ በጣም አመስግነዋቸዋል፡፡ ሁሉም ሠራተኛ ሥራውን፣ መብቱንና ግዴታውን፣ አውቆ የሚሠራ ምስጉን ሠራተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም የተጀመሩትን መሠረተ ልማቶች በአዲሱ አስተዳዳሪ በሊቀስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቁ ጽኑ እምነታቸው መሆኑን አክለው ገልፀዋል፡፡

 

በስተመጨረሻ የተደረገላቸውን አቀባበል በማስመልከት ንግግር ያደረጉት ክቡር ሊቀስልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ ሲሆኑ የተደረገላቸውን አቀባበል ካመሰገኑ በኋላ ካቴድራሉ ዓለም አቀፋዊ እንደመሆኑ መጠን በልማትና በመልካም አስተዳደር ወደተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ የሁሉም ሠራተኛና ምእመን አስተዋጽኦ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከዚሁ ጋር አያይዘው ዘመኑ በሚፈቅደው አስተሳሰብና አሰራር ሰዎች መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡ አገሮችና ሰዎች የሚያድጉት በሥራና በሥራ ብቻ መሆኑንና እግዚአብሔርም የሚወደው መልካም ሥራ መሆኑን አብራርተው ገልፀዋል፡፡

 

በመሆኑም ሁሉም የካቴድራሉ ሠራተኛና ምዕመናን በእውቀታቸውና በገንዘባቸው ለቤተክርስቲያን እድገትና ልማት ከጐናቸው እንዲሰለፉ ጥሪያቸውን አስተላልፏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የካቴድራሉ ሰበካ ጉባዔ፣ አስተዳደር ሠራተኞች፣ ማህበረካህናትና ልዩ ልዩ ሠራተኞች በካቴድራሉ ሁለገብ አዳራሽ ትውውቅ ተደርጓል፡፡ አንዳንድ የቤተክርስቲያኑ ሠራተኞችና ምዕመናን እንደገለጹት እኚህ መንፈሳዊ አባት ለሰባት ዓመት ያህል በቆዩበት በደበረ ገነት መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እጅግ በጣም አስደናቂ ሥራ መሥራታቸውንና ለዚሁ ታላቅ ካቴድራል የተመረጡትን በዚሁ ልማታዊ ሥራቸው መሆኑ ተናግሯል፡፡ እንደዚሁም አንዳንድ ነባር የካቴድራሉ ሠራተኞች ሊቀሥልጣናት አባ ገ/ማርያም አጽብሐና ሌሎች ለዚሁ ካቴድራል ትልቅ ሥራ ሠርተው የሄዱት ወሳኝ የልማት አባቶች አስተዳዳሪዎችን ሊተኩ እንደሚችሉና ብሎም የላቀ ሥራ ሊሠሩ እንደሚችሉ ትልቅ ተስፋ ተጥሎባቸዋል፡፡ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸውም ሁሉም የካቴድራሉ ሠራተኞች ተመኝተውላቸዋል፡፡

 

በሌላ ዜና የቀድሞ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ የነበሩትን ሊቀሊቃውንት አባ ጥዑመልሳን ኪ/ማርያም በካቴድራሉ ጽ/ቤት፣ ካህናትና ልዩ ልዩ ሠራተኞች አማካኝነት በዓይነቱ ልዩ የሆነ አሸኛኘት በካቴድራሉ ሁለገብ አዳራሽ የካቲት 1ዐ ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም. ተደርጉላቸዋል፡፡ በዚሁ ዕለት ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ ሊቀሥልጣናት አባ ገ/ሥላሴ በላይ የካቴድራሉ አስተዳዳሪና ጥሪ የተደረገላቸው የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የካቴድራሉ ካህናትና ልዩ ልዩ ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን በካቴድራሉ ሠራተኞችና ጽ/ቤት አማካኝነት የተዘጋጀውን ሽልማት በብፁዕ አቡነ አረጋዊ አማካኝነት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በማግስቱ የካቲት 11 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም. ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ አዲሱ የካቴድራሉ አስተዳዳሪ፣ የተለያዩ አስተዳዳሪዎች፣ ልብሰተክህነት የለበሱ የካቴድራሉ ካህናትና መዘምራን ከሌሊቱ 1ዐ፡3ዐ ላይ አባ ጥዑመልሳን ኪ/ማርያምን አጅበው ታዕካ ነገስት ባዕታ ለማርያም ገዳም የተገኙ ሲሆን የገዳሙ የቀድሞ አስተዳዳሪ የነበሩት ሊቀሊቃውንት አባ ዘርዓዳዊትና ልብሰተክህኖ የለበሱ የገዳሙ ካህናትና ዲያቆናት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ ሥርዓተ ቅዳቤውም በክቡር ሊቃ ሊቃውንት አባ ጥዑመልሳን ኪ/ማርያምና በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ካህናት መሪነት የተከናወነ ሲሆን ከቅዳሴ በኋላ በአሉን አስመልክቶ በአውደ ምህረቱ ላይመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እና ታዕካ ነገስት ባዕታ ለማርያም ገዳም ሊቃውንት ቅኔ ቀርቦ የበአሉ ፍፃሜ ሆኗል፡፡

 ዲ/ን ዘሩ ብርሃኔ

የ2004 የጥምቀት በዓል በካቴድራሉ መሪነት በድምቀት ተከበረ

በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

ጥር 12/2004ዓ.ም

በየዓመቱ ጥር 10 እና 11 የሚከበረው  የጌታችን  የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥመቀት በንበረ ፀባኦት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል መሪነት ከ13 ታቦታት በላይ በሚያድሩበት በጃን ሜዳ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት  የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንትና ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ  ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም በደመቀ  ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡፡

የዓመቱ ተረኛ የሆነው የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን መዘምራን ዕለቱን በማስመልከት ያሬዳዊ ዝማሬ ‹‹ ተሰሃልከ እግዚኦ ምደረከ ሃሌ ሉያ ወረደ ወልድ እም ሰማያት ውስተ ምጥማቃት በፍስሐ ወበሰላም››በማለት ያሬዳዊ ዜማ  አቅርበዋል፡፡

በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ዐበይት በዓላት ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል የጥምቀት በዓል አንዱ ነው፡፡ይህም በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ፤ በማእከለ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን  ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በየዓመቱ ከዋዜማው ከጥር 10 ጀምሮ በደመቀ ሁኔታ በማክበር ላይ ትገኛለች፡፡ ለእኛ አብነት ይሆነን ዘንድ፤ የእዳ ደብዳቤያችንን እንደ ገል ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ በደላችንን ይደመስስ ዘንድ ጌታ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይህንን መሠረት በማረድግ በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚገኙ ታቦታት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ በካህናትና ዲያቆናት፤ እንዲሁም በሰንበት ት/ቤቶች መዘምራንና ምዕመናን በዝማሬ በመታጀብ በአቅራቢያቸው ወደሚገኘው ታቦት ማደሪያ በማምራት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በመሔድ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ማምራቱን ያበስራሉ፡፡ ‹‹ያን ጊዜም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ናዝሬት መጣ ዮሐንስም በዮርዳኖሰ ወንዝ አጠመቀው›› እንዲል፡፡/ማቴ.3፡1/
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መስራቿን መድኅነ ዓለም ክርስቶስን ለዓለም የምትሰብክበት፣ ከእርሱም ያገኘችውን፣ ይህም ዓለም እንደሚሰጠው ያልሆነውን፣ የእግዚአብሔር ልጅነት፣ ሰላም፣ ፍቅርና ትሕትና ለዓለሙ ትሰብክበታለች፡፡ እንዲሁም ለሀገራችን በጎ ገጽታን በመፍጠር ረገድ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ ጎብኚዎች ተደንቀው የሚያዩትና አንዳንዶች ልባችውን ለእውነት ክፍት ያደረጉ የሚያምኑበት በመስተንግዶው የሚደመሙበት በመሆኑ ሃይማኖታዊ በዓሉን በልዩ ትኩረት ታከብራለች፡፡

ለዚህ በዓል አከባበር ቤተክርስቲያን ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ ታቦታት በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲመለሱ ጉልህ ሚናዋን ትወጣለች፡፡ በዚህ መሠረት  በየአጥቢያው የሚገኙ ወጣቶች ከክብረ በዓሉ ቀደም ብሎ ለሐላፊነት በመሰብሰብ ቅዱሳት ሥዕላትን በታቦታት ማረፊያዎች በማዘጋጀት፣ በተለያዩ ህብረ ቀለማት ያሸበረቁ ጨርቆችን /ባነሮችን/፤ የኢትዮጵያ ባንዲራን በየአብያተ ክርስቲያናቱ አደባባዮች በመስቀል፣ የቤተክርስቲያናትን ቅጥርና አስፋልት በማጽዳት ፤ለታቦት ክብርን ለመስጠት ምንጣፎችን በማንጠፍ በዓሉን ያደምቁታል፡፡
ምእመናን ከየቤታቸው ለበዓሉ በሚገባው ልብስ አሸብረቀው ወጥተዋል፡፡ እናቶቻችን ከየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ የሚሰሙትን የሊቃውንት አባቶቻችን ወረብ ተከትልው፣ የታቦታቱን መውጣት በመጠባበቅ እልልታቸውን ያሰማሉ፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችም ዝግጅቶቻቸውን አጠናቅዋል፣ የዝማሬ ልብሳቸውን ለብሰዋል፡፡ የሻሂ የእረፍት ሰዓታቸውን በመጠቀም ከየመሥሪያ ቤታቸው በር ላይ የታቦታትን ማለፍ በእነርሱም መባረክን ዓይናቸው ተስፋ እያደረገች ታቦታቱ የሚመጡበትን አቅጣጫ ያማትራሉ፡፡
ከሰዓት በኋላ በነበረው መርሐ ግብር በተለይም በጃንሜዳ ከየአድባራቱ አስራ ሦስት ታቦታት በአንድነት የሚገኙበት በመሆኑ ህዝቡን ለመባረክ የተገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተ/ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት የዓለም ሐይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ከብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን፤ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ልብሰ ተክህኖ ለብሰው ፤በመዘምራንና ምዕመናን በመታጀብ ጉዞ የተጀመረ ሲሆን አመሻሽ ላይ ጃን ሜዳ ሊደርሱ ችለዋል፡፡ የየሰንበት ት/ቤቶቹ መዘምራን ፤ የማኅበረ ቅዱሳን መዝሙር ክፍል አባላት ያሬዳዊ ዜማ እየዘመሩ ፤ምዕመናን በዕልልታና በሸብሸባ ታቦታቱን በማጀብ በዓሉን አድምቀውታል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከጋዜጠኞች ለቀረበ ጥያቄ እለቱን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ‹‹የዛሬው በዓላችን በሃይማኖታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ጸጋና በረከት የምናገኝበት፤ ሁላችንም በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የምንወለድበት፤ ልጅነት የምናገኝበት በዓል ነው፡፡›› በማለት  ገልጸዋል፡፡

በበዓሉ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ከውጭ ሀገር በዓሉን ለመከታተል የመጡ እንግዶችና ቱሪስቶች የተገኙ ሲሆን   በብጹዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገሪማ ሰፋ ያለ  ቃለ እግዚአብሔር  ተሰጥቷል፡፡ በመጨረሻም በብጹዕ አቡነ ጳውሎስ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ተሰጥቶ ታቦታቱ ወደ ተዘጋጀላቸው ማረፊያ ቦታ ገብተዋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የዓጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊው በዓል በድምቀት ተከበረ

በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

ጥር 7/2004ዓ.ም.

በየዓመቱ ከልደት ቀጥሎ ጥር 7 ቀን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚከበረው ዓመታዊው   የሥላሴ በዓለ በዚህ ዓመትም በንበረ ፀባኦት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት  የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንትና ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም በደመቀ  ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡፡

በዓሉ መከበር የጀመረው ከዋዜማው ከጥር 6 ጀምሮ ሲሆን የካቴድራሉ ካህናትና መዘምራን ከዋዜማው ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ለ48 ሰዓታት ሌሊትና ቀኑን ሙሉ ያለ ማቋረጥ ስብሃተ እግዚአብሔር ሲያቀርቡ ውለው አድረዋል፡፡

ይህ መንፈሳዊ አገልግሎት ማለትም ስርዓተ ማህሌተ፣ስርዓተ  ቅዳሴ እንዲሁም ሰዓታትና ሰርክ ፀሎት በአጠቃለይ የስርዓተ አምልኮ አፈፃፀም  በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ልዩ በመሆኑ የእምነቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም እጀግ በጣም የሚስደንቅ ነው፡፡

ቀደም ሲል የተከበረው የጌታችን  የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ይህን በመሰለ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን በፊታችን በታላቅ ድምቀት በየዓመቱ ጥር 10 እና 11 የሚከበረው  የጌታችን  የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥመቀትም በካቴድራሉ መሪነት ከ11 ታቦታት በላይ በሚያድሩበት በጃን ሜዳ እንደሚከበር የቤ/ክርስቲያኑ አስተዳደር አሳውቋል፡፡

 

tourism-news

የሁለትዮሽ ውይይት ከኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር

tourism-newsየቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ካቴድራሉን የቱሪስት መድረሻነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ይቻል ዘንድ የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን የካቴድራሉ የሰበካ ጉባዔ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ እንደ ጽ/ቤቱ መግለጫ አሰራሩን ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ከአገር ገጽታ ግንባታ ላይ የበኩሉን ለመወጣት ያግዝ ዘንድ የካቴድራሉ ቱሪዝምና ቅርስ ጥበቃ ክፍል በአዲስ መልክ ኮሚቴዎች አቋቁሞ የአጭርና የረጅም ዕቅዶችን በማውጣት ስራውን በይፋ ጀምሯል፡፡

  • በተያያዘ ዜና የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሙሉ ታሪክ የሚያሳይ DVD ከባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለካቴድራሉ ተበርክቷል፡፡
  • በሌላ ዜና የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በአገር ግንባታ ሒደት ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ በኃይሌ ገብረሥላሴ ጐዳና በተለምዶ ሃያ ሁለት በሚባል አካባቢ በአርባ አምስት ሚሊዮን ብር ወጪ ዘመናዊ ሁለገብ ህንፃ እየገነባ መሆኑን  የሰበካ ጉባዔ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
  • በአሁኑ ወቅትም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በአዲስ መልክ ለማሠራት ፕላኑንና ዲዛይኑን ሁሉ አልቆ ከክፍለ ከተማ ፈቃድ እየተጠባበቀ መሆኑንና ሥራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡
banner

መ/ጸ/ቅ/ስላሴ ካቴድራል አዲስ ድረገጽ አሰራ

banner

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል በዘመናዊ መልኩ የተዋቀረ አዲስ ድረገጽ በማሰራት በስራ ላይ አዋለ።

ድረገጹ ኢ.ኤ.ኤስ. ሶፍትዌር ቴክኖሎጂስ በተባለ ድርጅት የተሰራ ሲሆን የዲዛይን ጥራቱን ጠብቆ የመረጃ ጥንቅሩንም ለተጠቃሚዎች በቀላሉ ለመጠቀም እንዲያስችል ተደርጎ ተሰርቷል::