5.3

ዓመታዊው የዓጋዓዝተ ዓለም ሥላሴ ክብረ በዓል በድምቀት ተከበረ

                        እንኳን ለአብርሃሙ ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና በሕይወት አደረሳችሁ፡፡

                          በመ/ር ዘሩ እና በመ/ር ዳዊት

5.3

‹‹እመ እግዚአብሔር ኢሐነፀ ቤተ ከንቶ ይፃምው እለ የሃንፁ›› ‹‹እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ግንበኞቹ በከንቱ ይደክማሉ›› መዝ 126፡1 ይህን የታላቁን ነቢይ ቃል ለመነሻነት የተመረጠው ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው የአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በዓለ ንግሥን ምክንያት ለመግለፅ ነው፡፡ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ዳዊት ምንም እንኳ ይህን ኃይለ ቃል ከጊዜ በኋላ የፃፈው ቢሆንም የዚህን ጽሑፍ ሐሳብ የሚያንፀባርቀው ቀደም ሲል በዘመነ ህገ ልቡና የተፈፀመ ነበረ በዘፍ1ዐ፡32 ላይ ‹‹የኖኀ የልጆቹ ነገዶች እንደየ ትውልዳቸው በየህዝባቸው እነዚህ ናቸው፤ አህዛብም ከጥፋት ውኃ በኋላ በምድር ላይ ከነዚህ ተከፋፈሉ››፡፡ ይልና በተለይ በዘፍ 11፡1 ጀምሮ ያለውን ስንመለከት ደግሞ ‹‹ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋ ንግግር ነበረች›› ብሎ የሰናኦርን ግንብ መገንባትና መፍረስን ያትታል፡፡ በአጭሩ የዚህ ኃይለ ቃል ጭብጥ ሐሳብ፡- የሰው ልጆች እግዚአብሔርን ለመቃወም ሲሉ ታላቅ ግንብ እንደገነቡና እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ታላቅ ግንብ እንደ አፈራረሰባቸው ነው የሚያብራራው፡፡ ይህን ግንብ ለመገንባት 43 ዓመት ፈጅቶባቸዋል፡፡

ይህ ግንብ በአሁኑ ዘመን በነዱባይ ከተገነቡት ታላላቅ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች እንደሚበልጥ የቤተ ክርስቲያኒቱ መምህራን ይናገራሉ፡፡ ይህንን ህንፃ ሲገነቡ የነበሩ ሰዎች ቀደም ሲል እንደተገለፀው ለትምክህትና እግዚአብሔርን ለመቃወም ስለሆነ እግዚአብሔር ደግሞ ትምክህትንና ራሱ እግዚአብሔርን የሚቃወም ሰው አይወድም ዘዳግ 5÷ 10 አስመ አነ አምላክ ቀናኢ እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝ ሲል በሙሴ አፍ እንዳስተማረ የሚቃወሙትን የቃወማቸዋል ፡፡

03

የልደት በዓል በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቅት ተከበረ

                                                                                                     በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

 እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት ተወልዶላችኋል ሉቃ.2፥11

እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ፡፡

03

የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ታላላቅ በዓላቶች መካከል አንዱ ሲሆን ሁሌ በየዓመቱ ታኅሣሥ 29 እንደሚከበር ይታወቃል፡፡ እንደ ተለመደው የዘንድሮ በዓልም መከበር የጀምረው ከዋዜማው 12.00 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትና አድባራት ሥራዓተ ማኅሌት፤ሰዓታት እና ሥርዓተ ቅዳሴ ሲከናወን ያድራል ፡፡ በተለይም በአገሪቱ ዋና መዲና በሆነቸው በአዲስ አበባ ከተማ በሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሚገኘው በመንበረ ጸባዖት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል በዓሉ እጅግ በጣም በማቅ ሁኔታ ተከብሮ አድሯል፡፡በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፤ ዶ/ር ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ፤ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ፤በፁዕ አቡነ አረጋዊ የመንበረ ጸባዖት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ኃላፊ ፤ካህናት እና በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በበዓሉ ላይ ተኝተው በዓሉን በድምቀት አክብረዋል፡፡በዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል መልካም ፈቃድ ሥርዓተ ቅዳሴውን የመሩት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሲሆኑ በ3ቱም መንበር በሥላሴ፤በማርያምና በዮሐንስ ቤተ መቅደሶች ቅዳሴው የተቀደሰ ሲሆን ሥርዓተ ቅዳሴውም በተለመደው ሰዓት ተጠናቅቋል፡፡ በበዓሉ ላይ ለተገኙ መዕመናን በዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል አማካኝነት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ተሰጥቶ የበዓሉ ፍፃሜ ሁኗል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሁሌ በየዓመቱ የሚከበረው የቅዱስ በዓለ ወልድ በዐለ ንግሥ ታኅሣሥ 29/2005 ዓ.ም በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ቅዱስ በዓለ ወልድ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ታላላቅ ገዳማትና አድባራት መካከል አንዱ ሲሆን የተመሠረተውም በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን መንግስት በ1883ዓም እንደሆነ ይታወቃል፡፡

abune_nathnael

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የገና 2005ዓ.ም በዓለ ልደት ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡

                                                                                                      በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

abune_nathnael
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል መግለጫ ሲሰጡ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት “በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ እንዲሁም የሕግ ታሪሚዎች ሆናችሁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት እንኳን ለ2005 ዓ.ም. የጌታችን የአምላካችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዐለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ፡፡” ካሉ በኋላ “በጌታችን ቤዛነት እንድን ዘንድ አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮአልና፤ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር በዚህ አውቀናል፡፡ እግዚአብሔር ከፍጡራን ሁሉ የተለየና ከአእምሮ በላይ የሆነ መለኮታዊ ኀይል ያለው አምላክ በመሆኑ የባሕርዩን ጥልቅነት በምልአት ማወቅ ፈጽሞ የማይቻል ቢሆንም እርሱ ራሱ በገለጸልን መጠን የተወሰኑ ነገሮችን እናውቃለን፡፡

02

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ3ኛ ጊዜ እረዳታ ተሰጠ

ከአሁን በፊት በዌብሳይታችን አማካኝነት ወጣት ብሩክ አስራት ከዛሬ 3 ወር በፊት ጀምሮ ለካቴድራሉ አረጋውያን የሚሆን በየወሩ ለአረጋውያኑ የሚያስፈልጋቸውን የምግብ እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ስንዘግብ መቆየታችን የሚታወስ ሲሆን አሁንም እንደተለመደው ለ3ኛ ጊዜ ለገና በዓል መዋያ የሚሆን፡-    25 ሌትር ጋዝ፤     15 ሌትር ዘይት    15 ኪሎ ስኳር፤    15 ኪሎ በርበሬ፤     15 ኪሎ ሽሮ፤5 […]

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ልዩ እድሳት እንደሚያስፈልገው ተገለፀ፡፡

                   በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት እንደገለፀው የካቴድራሉ ህንፃ ወስጣዊም ሆነ ውጫዊው ክፍሉ ከጊዜ ብዛት የተነሳ የመሰነጣጠቅ ሁኔታ እየታየበት በመምጣቱ አስቸኳይ የሆነ ሙሉ እድሳት እንደሚያስፈልገውና ጥናቱ በጥንቃቄ እንዲጠና ከበላይ አካልም ጭምር ስለታነበት በባለሞያዎች በምን ዓይነት ሁኔታ መታደስ እንዳለበት ከመጋቢት 2ዐዐ4 ዓ.ም ጀምሮ ጥንቃቄ በተሞላበት ሙሉ ጥናት ሲደረግበት ቆይቶ […]

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን ለ2ኛ ጊዜ የምግብ እህል እረዳታ ተሰጠ

    የዛሬ ሁለት ሣምንት አካባቢ ወጣት ብሩክ አስራት ከአሜሪካን አገር መጥቶ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በንግስት ዘውዲቱ መታሰቢያ ቤት ተጠልለው ለሚኖሩ 15 አረጋወያን በአካል ተገኝቶ የአረጋውያኑ የአኗኗር ሁኔታ እንደጎበኘና ለጊዜው የሚስፈልጋቸውን ልዩ ልዩ የአንድ ወር የምግብ አስቤዛ እርዳታ እንዳደረገላቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡     አሁንም ከአገር ቤት ተመልሶ ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ቀደም ሲል ቃል […]

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ 15 አረጋወያን እረዳታ ተሰጠ

          በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ “ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፡፡” መዝ. 40¸1 “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ”2ኛ ቆሮ. 9¸7 እርዳታውን የሰጠው በአሜሪካን አገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊው ወጣት ብሩክ አስራት ነው፡፡ወጣት ብሩክ አስራት አረጋውያኑ የሚኖሩበት የንግስት ዘውዲቱ መታሰቢያ ቤት ተገኝቶ የአረጋውያኑ የአኗኗር ሁኔታ የጎበኘ/የተመለከተ ሲሆን በየሳምነቱ ሰኞ፤ረቡዕና ዓርብ በካቴድራሉ በኩል ለእያንዳንዳቸው 2 እንጀራ እንደሚሰጣቸውና ለዙሁም […]

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሠራተኞች የአስተዳደርና የቅርስ አያያዝ ስልጠና ተሰጠ

                          በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ መስከረም 18/01/05   ይህ ስልጠና የተዘጋጀው በካቴድራሉ አስተዳደር ጽ/ቤት አማካኝነት ሲሆን ለዚሁ ስልጠና እንዲሰጡ የተጋበዙ ምሁራን አሰልጣኞች፡- 1ኛ. ዶ/ር አባ ኃለማርያም መለሰ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን 2ኛ. መ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ የቅርሳቅርስና ቤተመዘክር ኃላፊ ሲሆኑ በተቀመጠላቸው መርሃ ግብር መሠረት በተሠጣቸው ርዕስ ስልጠናውን/ትምህርቱን በሚገባ ሰጥተዋል/አስተምረዋል የአስተዳደርና የቤተ ክርስቲያን አገልገሎት በተመለከተ […]

የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ

ነሐሴ 27ቀን 2004 .

በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ስነስርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ነሐሴ 27 ቀን 2004 . ከቀኑ 10 ሰዓት ተፈጽሟል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የቀብር ስነ ስርዓት በተመለከተ ከንጋቱ 11 ሰዓት በታለቁ ቤተ መንግስት ፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ስራአስከያጅ፣6 የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ካህናት ጋር በህብረት ሙሉ ፀሎተ ፍትሐት አድርሰዋል በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ከ15/2004 ዓ.ም መሐራ እግዚኦ ለነፍሰ መራሔ መንግሥት ገ/ማርያም፤ አቤቱ የመራሔ መንግሥታችን የገብረ ማርያምን ነፍስ ማር” በማለት ጸሎትዋን አድርሳለች በማድረስ ላይም ትገኛለች፡፡በተለይም በ26/2004 ለ27 አጥቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከ600 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ካህናትና መዘምራን በህብረት ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ ሌሊቱን ፀሎተ ፍትሐት ሲያደርሱ አድረዋል፡፡

በታላቁ ቤተ መንግስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የህዝብ ተወካዮች /ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመከላከያና የፖሊስ አባላት፣ ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡

በመስቀል አደባባይም 25 በላይ የሀገራት መሪዎችና ርዕሳነ ብሔራት እንዲሁም በርካታ የአህጉራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፣ የመከላከያና ፌደራል ፖሊስ ሰራዊት፣ የመንግስት ሰራተኞችና እንግዶች አስከሬኑን ለመቀበል በስፍራው ተገኝተዋል፡፡  

ክብርት ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን እንዳሉት መለስን ከልጅነቱ ጀምሮ ነው የማወቀው፡፡ ዱሮም ጀምሮ ህልሙ የነበረው በኢትዮጵያ ፍትህ፣ ሰላምና እድገትን ማስመዝገብ ነበር፡፡ ሁሌም ያልም የነበረው ድህነትን ስለመታገል ነበር፡፡ ጊዜውን ሁሉ ይሰጥ የነበረው ህልሙን ለማሳካት ነበር፡፡ ልጆቼም የሚፈልገውን ጊዜ አልነፈጉትም፡፡ መለስ ለፍትህ፣ ለሰላምና ለፍቅር የቆመ ነበር፡፡ ይህንንም የኢትዮጵያ ህዝብ በማረጋገጡ በጣም አመሰግናለሁ ፡፡

እኔም ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ሆኜ እሱ የጀመራቸውን የልማት ተግባራት ለማስቀጠል የበኩሌን አስተዋፅኦ አበረክታለሁ ብለዋል፡፡

8 ሰዓት 25 ደቂቃ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የደረሰ ሲሆን፡፡ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራልም ለ30 ደቂቃ ያህል ደውል የተደወለ ሲሆን አስከሬኑም ከሰረገላው ወርዶ ወደተዘጋጀለት ልዩ የፀሎት ቦታ አርፏል፡፡ በካቴድራሉ ካህናትና መዘምራንም ስርዓተ ፀሎት ተካሂዷል፡፡

 

9 ሰዓት 10 ደቂቃ ላይ የፀሎት ስነ ስርዓት እንደተፈፀመ አስከሬኑ ቤተ ክርስቲያኑን በቀኝ በመዞር 9 ሰዓት 25 ደቂቃ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን ወደተዘጋጀለት የቀብር ቦታ ያረፈ ሲሆን፤የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀብር ስነ ስርዓት መጠናቀቁን በማስመልከት 21 ግዜ መድፍ ተተኩሷል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አጭር የህይወት ታሪክ

 

የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

  ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሥርዓተ ቀብራቸው ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ከፍተኛ […]

አስተያየትዎን ይጻፉልን