መፈለጊያ
በቅርብ የተለቀቁ
- የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተነ እንሠራለን መጽሐፈ ነህምያ ምዕ 2፡20
- የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከብሮ ዋለ።
- Pre-qualification of Companies for the Renovation Works of Holy Trinity Church in Addis Ababa, Ethiopia
- Pre-qualification of Companies for the Renovation Works of Holy Trinity Church in Addis Ababa, Ethiopia
- of Holy Trinity Church in Addis Ababa, Ethiopia
- ዓመታዊው የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ
- ወርሐዊ የአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ክብረ በዓል ባማረ ሁኔታ ተከበረ
- በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቅጽረ ግቢ ጸረ ተዋህስያን ኬሚካል ተረጨ
- በወቅታዊ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ
- በዓለ አስተርእዮ
የ2004 የጥምቀት በዓል በካቴድራሉ መሪነት በድምቀት ተከበረ
በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ
ጥር 12/2004ዓ.ም
በየዓመቱ ጥር 10 እና 11 የሚከበረው የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥመቀት በንበረ ፀባኦት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል መሪነት ከ13 ታቦታት በላይ በሚያድሩበት በጃን ሜዳ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንትና ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡፡
የዓጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊው በዓል በድምቀት ተከበረ
በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ
ጥር 7/2004ዓ.ም.
በየዓመቱ ከልደት ቀጥሎ ጥር 7 ቀን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚከበረው ዓመታዊው የሥላሴ በዓለ በዚህ ዓመትም በንበረ ፀባኦት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንትና ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡፡
የሁለትዮሽ ውይይት ከኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር
ዝቋላ ገዳም
የዝቋላ አቡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በ1168 ዓ.ም. ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ በነበሩበት ጊዜ ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ቅዱሳት በሆኑ እግሮቻቸው በመርገጥና በመባረክ በተራራው አናት ላይ በሚገኘው ውብና ማራኪ በሆነው ባሕር ውስጥ ለ1)///1ዐዐ ዓመታት በመጸለይ ከዘለዓለማዊው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማይታበል ሕያው ቃል ኪዳን የተቀበሉበት በ04//14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ጽላታቸው የተቀረጸበት ቤተክርስቲያናቸው የታነጸበት በክቡር ስማቸው ገዳም የተመሠረተበት አምላከ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ብርሃነ ረድኤቱን በየጊዜው የሚገልጥበት በሀገራችን ኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉት ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት አንዱ ነው፡፡
የዚህን ታላቅ ገዳም አመሠራረትና ታሪክ እንዲሁም መልክአ ምድር አቀማመጡን በመጠኑ ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡
መ/ጸ/ቅ/ስላሴ ካቴድራል አዲስ ድረገጽ አሰራ
የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል በዘመናዊ መልኩ የተዋቀረ አዲስ ድረገጽ በማሰራት በስራ ላይ አዋለ። ድረገጹ ኢ.ኤ.ኤስ. ሶፍትዌር ቴክኖሎጂስ በተባለ ድርጅት የተሰራ ሲሆን የዲዛይን ጥራቱን ጠብቆ የመረጃ ጥንቅሩንም ለተጠቃሚዎች በቀላሉ ለመጠቀም እንዲያስችል ተደርጎ ተሰርቷል::