የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ስብከተ ወንጌል

መግቢያ፡- ስብከተ ወንጌል ማለት ምን ማለት ነው ስብከተ ወንጌል ማለት የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን፣ የሰውን ልጅ ወደ ቀደመ ክብሩ (ልጅነቱ) መመለስ የሚያበሥረውን ቃል ማብሠር፣ ማስተማር፣ ማሳመን….ማለት ነው፡፡ ይኸውም በደመ ወልደ እግዚአብሔር የተዋጀችው ቤተክርስቲየን ዕለት ዕለት የምትታነጽበት ቃል ወንጌል ነው፡፡ የስብከተ ወንጌል ዓላማ ዋናው የስብከተ ወንጌል ዓላማ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወራሽ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ […]

አገልግሎቶች

ሁለገብ አዳራሽ ይህ አዳራሽ በሊቀ ሥልጣናት አባ ገብረ ማርያም አጽብሐ የተሠራ ሲሆን እጅግ ዘመናዊ እቅድን ተከትሎ የተሠራ ሆኖ ለሠርግ፣ ለስብሰባ፣ ለሙት ዓመት፣ መታሰቢያና ለመሳሰሉት አገልግሎቶች፣ ለአገልጋዮች በነፃ አገልግሎት ሲሰጥ ለውጭ ሰዎች ደግሞ በገንዘብ ይከራያል፡፡ ከአዳራሹ ጋር ተያይዞ የተሠራው የፉካ መቃብርም ለ7 ዓመታት ውል እየተከራየ የካቴድራሉን ገቢ በማሳደግ ላይ ከመሆኑም ሌላ አብሮ የተገነባው ፎቅም ለልዩ ልዩ […]

ሰንበት ትምህርት ቤት

ሰ/ት/ቤት በዘመነ ብሉይ የሰንበት ት/ቤት ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ የነበረው ነው፡፡ ለምሳሌ በዘዳግም “እነዚህ ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው በአይኖቻችሁም መካከል እንደክታብ ይሁን ልጆቻችሁንም አስተምሩአቸው በቤትህም ስትቀመጥ በመንገድህም ስትሄድ ስትነሳም አጫውታቸው” የሚል እናነባለን (ዘዳ 1÷6-9)ከዚህ በላይ እንደተጠቀሰው እስራኤላውያን ልጆቻቸውን ሕገ እግዚአብሔር እንዲያስተምሩአቸው ታዘዋል በትእዛዙም መሰረት ሕፃናቶቻቸውን በቤተ እግዚአብሔርና በቤታቸው ሕገ ኦሪትን እያስተማሩ […]

የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ት/ቤት

በ1955 ዓ.ም. መስከረም 14 ቀን በማታ ፕሮግራም ሥራውን የጀመረው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ት/ቤት በወቅቱ የተቀበላቸው ተማሪዎች 8 ብቻ ሲሆኑ እነዚህን መነኮሳትና ዲያቆናት ነበሩ፡፡ በ1956 ዓ.ም. ከ1ኛ እስከ 4ኛ ባሉ ቁጥራቸው 39 የሚደርሱ ተማሪዎችን ይዞ የመደበኛ ትምህርት ጀመረ፡፡ በዚያን ጊዜ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ት/ቤት “የኢትዮትያ ኦርቶዶክስ ሐዋርያዊ ድርጅት” በመባል ይታወቅም ነበር፡፡ ት/ቤቱን ለመክፈት ያስፈለገበት ዓላማም የቤተ […]

የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ መዘክር (ሙዚየም)

አደረጃጀትና ይዘት በአጭሩ ቀደም ባሉት ጊዜያት ካቴድራሉ በሙዚየምነት ሲጠቀምበት የነበረው ከካቴድራሉ ቤተ መቅደስ አንደር ግራውንድ (ምድር ቤት) የሚገኘውን የዕቃ ግምጃቤት እንደ ነበረ ቀደምት ታሪኩን እናስታውሳለን፡፡ ይህ ደግሞ ከምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን መጠበቅና ሥርዓት አንፃር ቦታው ለጉብኝቱ ሂደት አመች አልነበረም፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ባላቸው ፅኑዕ እምነት፣ ለቱሪዝም ዕድገትና መስፋፋት በነበራቸው ከፍ ያለ ራዕይና ከውጭው ዓለም ተሞክሮ […]

Charity

  {gallery}pic-charity{/gallery} The Holy Trinity Cathedral charity was established during the time of Emperor Haileselassie. It is still in existence helping the needy. During the time of the former king, he was providing Fund worth enough to feed and cloth the poor. But after the dethronment of the Emperor, things have become different and the […]

የልማት እንቅስቃሴዎች

ካቴድራሉ በልማት በኩል የተከተለው አቅጣጫ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሁሉም አቅጣጫ መሪ እንደመሆኑ መጠንና አስተዳደራዊ ይዘቱም ሰፊ በመሆኑ ገቢው ያኑ ያህል በቂ መሆን ስለሚገባው ከመንግሥት ከተሰጠው ጋሻ መሬት በተጨማሪ ት/ቤት፣ የሙካሽ ሥራ፣ የሥጋጃ ሥራ፣ የአልባሳት ማዘጋጃ፣ የመጻህፍት ማዘጋጃ እና በነዚህ ክፍሎች የተዘጋጁትን የምርት ውጤቶች ለሕዝብ በማቅረብ የሚከፋፈሉባቸው ሱቆች ከአዲስ አበባ እስከ ክ/ሀገር አቋቁሞ ነበር፡፡ […]

የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት

ይህ ክፍል ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣እንደ አጽዋማት፣ ታላላቅ በዓላት እና የመሳሰሉትን መርሐግብሮች ጊዜውን ጠብቆ ፕሮግራም በማውጣት ሕዝቡን የሚያገለግል ሆኖ በተጨማሪም ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ዕለቱንና ሰዓቱን  ጠብቀው እንዲፈጽሙ መዘምራኑን፣ ልዑካኑንና ተጓዳኝ አገልጋዮችን የሚመራና የሚቆጣጠር የመንፈሳዊ አገልግሎት ክፍል ነው፡፡ የቤተክርስቲያኑ ሥዩማን የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሕዝቡን በሠለጠነ መንገድ ለማገልገል እንዲቻል የሚከተሉት የቤት ክርስቲያን ሥዩማን አሉት፡፡ ሥራቸውም የቤተ እግዚአብሔር […]

አስተዳደራዊ መዋቅር

እንደዘመናዊነቱ ሁሉ አስተዳደሩም በዚሁ እቅድ እንዲመራ የካቴድራሉ አመራር በሚከተለው መልክ ተደራጅቷል፡፡ {gallery}org-am{/gallery} 1. ሰበካ ጉባዔ፡- ይህ ክፍል ሌሎች ክፍሎችን የሚቆጣጠር ሆኖ የሁሉም ራስ የሆነው የካቴድራሉ ዋና ጽ/ቤት ነው፡፡ 2. የቤተክርስቲያን አገልግሎት፡- ይህ ክፍል ሥርዓተ ቤተክርስቲያን እንደ አጽዋማት፣ ታላላቅ በዓላት እና የመሳሰሉትን ጊዜውን ጠብቆ ፕሮግራም በማውጣት ሕዝቡን የሚያገለግል ሆኖ በተጨማሪም ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ሰዓቱን ዕለቱን […]

ቅ/ሥ/ካቴድራል

ቤተክርስቲያን የቤተክርስቲያን ቅድመ ታሪክ በአጭሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በርካታ ቋሚና ተንቀሳቃሽ የሆኑ ሃይማኖታዊ ትውፊትና ታሪካዊ ቅርሶችን ጠብቃ የያዘች ናት፡፡ ይህም ማለት በሕንጻ ግንባታና ከድንጋይ ተፈልፍለው የታነፁ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፡ ገዳማትና ታሪካዊ ሐውልቶች፣ የሥነ ጽሑፍ፣ የዕደ ጥበብ፣ የተለያዩ ንዋየ ቅዱሳትና የሌሎችም ቅርሶች ባለቤት መሆኗ ግልጽ ነው፡፡እነዚህ ደግሞ በዓለም አስደናቂ ከሆኑት ነገሮች መካከል በታሪካዊነታቸው ተመዝግበው የሚገኙ […]

የአስተዳዳሪው መልእክት

ከሁሉ አስቀድሜ የሥራና የጊዜ ባለቤት የሆነው አምላካችን እግዚአብሔር ለሀገርና ለወገን የሚጠቅም መልካም ሥራ የምንሠራበትን ጊዜ በቸርነቱ ስለሰጠን ክብርና ምስጋና ሁሉ ለእርሱ ይሁን፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሁለንተናዊ መልኩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያበረከተቺው አስተዋፅዖ ታሪክ የማይረሳው ፤ይልቁንም ታሪኩ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሳይቋረጥ ሲሻጋገር የሚኖር የታሪክ ባለቤት ናት፡፡  ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን በነበራቸው ከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን፣የሀገርና የህዝብ ፍቅር ዘመኑ በፈቀደላቸው መጠን ለሀገርና ለወገን የሚጠቅምና የሚያኮራ ሥራ በመሥራት ቤተ ክርስቲያናችን በመላው በዓለም ላይ ሐዋርያዊት፣ታሪካዊት እና ብሔራዊት እንድትሆን አስችለዋታል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ስሟ በቅዱስ መጽሐፍ ከ41 ጊዜ በላይ ተደጋግሞ የተፃፈው ሀገረ እግዚአብሔር በመሆኗ እና በክርስትና ሃይማኖቷ ቀዳሚ ሀገር ከመሆኗም በላይ የቀደምት የሥልጣኔ እና የሥነ–ጥበብ ባለቤት፤ እንዲሁም የሀገሪቱ ከፍተኛ የቱሪስት መስህብ ባለቤት በመሆኗ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ ሀገሪቱ የራሷ የሆነ ብቸኛ ፊደል እና የቀን አቆጣር እንዲኖራት ያስቻለች ከመሆኗም ባሻገር እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድርስ ብቸኛ የሀገሪቱ የትምህርት ተቅዋም/ትምህርት ሚኒስተር በመሆን ከፍተኛ የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ የተጨወተችው ሚና እንዲሁ በቃላት ብቻ የሚገላፅ አይደልም፡፡

የቤተ ክርስቲያን ህልውና በትምህርተ ወንጌል ላይ የተመሠረተ ስለሆነ ዘወትር መግቦቷን ሳታቋርጥ በካህናት አገልጋዮቿ ሌሊት በሰዓታት፣ በማኅሌት፣ በስብሐተ ነግህ እና በሌሎችም መንፈሳዊ ሥራዎች ሁሉ የምትሰጠው አገልግሎት በቀላል የሚገመት አይደለም፡፡

ቅድስት ሥላሴ ካቴድራልም ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከመቸውም ጊዜ በተሻለ መልኩ የቤተ ክርስቲያኒቱና የህብረተሰቡን ፍላጎት ባማከለና ዘመኑ በሚጠይቀው መልኩ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት ፈተናዎችን ሁሉ ተቋቁሞ ሌት ተቀን ጠንክሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰበካ ጉባዔ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የገቢ ዕድገት በማሳየት በልማትና መንፈሳዊ ጉዞዎች እየተጠናከረ መጥቶ አሁን ካለንበት ደረጃ ሊደርስ ችሏል፡፡ ነገር ግን አሁንም ብዙ ሥራ እንደሚቀር አያጠራጥርም ፡፡

የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ልዕልና መገለጫ የሆነው ካቴድራሉ ቀደም ባሉ ጊዜያት ለመላዋ ኢትዮጵያ በአጭርና በመካከለኛ ሞገድ ብሥራተ ወንጌል በሚል ይታወቅ በነበረው ሬድዮ ጣቢያ በየቀኑ የሚተላለፉ ትምህርቶችን የሚያዘጋጁ ምሁራንን ያቀፈ የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ድርጅት በሚል ስያሜ ተቋቁሞ በዚሁ ካቴድራል እንደነበርና የስርጭት ሽፋኑም በመላዋ ኢትዮጵያና አፍሪካ በሙሉ እንዲሁም በእስያ አህጉራት የሚዘልቅ እንደነበር የታሪክ ማኅደራት ምስክሮች ናቸው፡፡

የሰው ልጅ ሲፈጠር በቦታ የሚወሰንና የሚገደብ ሆኖ በመፈጠሩ በሌላ ሥፍራ ያለውን ነገር ሁሉ በራሱ ማወቅ አይችልም፡፡ሆኖም የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን አዕምሮ በመጠቀም የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን ሠርቷል፡፡

ከእነዚህም መካከል አሁን በዚህ ዘመን የተጀመረው የመረጃ መረብ ቴክኖሎጂ አንዱ ተጠቃሻ ሲሆን ይህ ቴክኖሎጂ ትውልዱ ሲጠቀምበት በዓለማዊ ትምህርት ብቻ ተወስኖ እንዳይቀር መንፈሳዊ ትምህርትንም ለማስታላለፍ ጥሩ አማራጭ መንገድ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችንም በእውቀቱ የተካኑትን ልጆቿን በመጠቀም ዘመኑ ባስገኘው ቴክኖሎጂ ትምህርት እንዲተላለፍ መደረጉ ጠቀሜታው እጅግ የላቀ ነው፡፡

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራልም ዘመኑ ያስገኘውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ታሪካዊውንና ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለውን ካቴድራል አገልግሎቱን የበለጠ ለማሳደግና በመላው ለዓለም ለማስተዋወቅ እንዲረዳ ታስቦ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ ነበረውን ድረ-ገፅ በአዲስ መልክ ከጥር 7/2011 ዓ.ም ጀምሮ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ኦፊሻል ድረ-ገፅ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ እንዲውል አድርገናል፡፡

የዚሁ አገልግሎትም ዘመኑ ባስገኘው ቴክኖሎጂ በመጠቀም ስብከተ ወንጌልን እና የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ ለዓለም ሕዝብ በማዳረስ ዓይነተኛ መሣሪያ ሆኖ አገልግሎት መስጠት ሲሆን በተጨማሪም ድረ ገጹን በመጠቀም የቤተ ክርስቲያናችንን አኩሪ ታሪክ ፤ቅርስና ታሪካዊ ቦታዎችን ከማስተዋወቅ ባሻገር ወቅታዊ የሆኑ መንፈሳዊና ማኅበራዊ መረጃዎችን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በቀላሉ እንዲዳረስ በማድረግ ነው ፡፡
በአሁኑ ሰዓት የካቴድራሉ ድረ- ገጽ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ጠቃሚ የሆነ መረጃ ከመስጠቱም በላይ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች መረጃን በመስጠት ረገድ እጅግ በጣም አመርቂ የሆነ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
ሊቀሥልጣናት ቆሞስ አባ ገ/ዋህድ ገ/ኪዳን
የመ/ጸ/ቅ/ሥላሴ ካቴድሪል አስተዳዳሪ

በፌስቡክ ያግኙን

ግጻዌ

አስተያየትዎን ይጻፉልን