መፈለጊያ
በቅርብ የተለቀቁ
- የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተነ እንሠራለን መጽሐፈ ነህምያ ምዕ 2፡20
- የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከብሮ ዋለ።
- Pre-qualification of Companies for the Renovation Works of Holy Trinity Church in Addis Ababa, Ethiopia
- Pre-qualification of Companies for the Renovation Works of Holy Trinity Church in Addis Ababa, Ethiopia
- of Holy Trinity Church in Addis Ababa, Ethiopia
- ዓመታዊው የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ
- ወርሐዊ የአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ክብረ በዓል ባማረ ሁኔታ ተከበረ
- በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቅጽረ ግቢ ጸረ ተዋህስያን ኬሚካል ተረጨ
- በወቅታዊ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ
- በዓለ አስተርእዮ
ዓመታዊው የዓጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ክብረ በዓል በድምቀት ተከበረ
በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚከበረው ዓመታዊው የሥላሴ ክብረ በዓል በዚህ ዓመትም በመንበረ ጸባዖት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኩሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡፡ በዚሁ ዕለት አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በአብርሃም ቤት […]
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የ2011 ዓ.ም የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ300 ችግረኞች እርዳታ ሰጠ!!
“እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ” 2ኛ ቆሮ.9÷7 በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ምግባረ ሠናይ ክፍል መሪነት እና አስተባባሪነት ለ300 አረጋወያን ዘላቂና ለተወሱኑ ወራት ሊያቆይ የሚችል ለእያንዳንዳቸው በአይነት15 ኪሎ ፍርኖ ዱቄት፣3 ሌትር ዘይት እና 3 ኪሎ ስኳር ተሰቷል፡፡ ካቴድራሉ 15 አረጋወያን በመደበኛነት የሚጦራቸው ያሉት ሲሆን ከዚሁ በተጨማሪ ምእመናንን በማስተባበር ሁልጊዜ በየዓመቱ የትንሣኤን በዓል […]
Mrs. Hirut Visits Her Former School, Inspires Students
State Minister of Foreign Affairs of Ethiopia, H.E. Mrs. Hirut Zemene visited the Holy Trinity Cathedral Primary School in Addis Ababa, her former school, and shared her experiences to students. The visit is part of the government’s initiative to help inspire students and youth. Noting that today’s youth are tomorrow’s leaders, Mrs. Hirut told students that […]
የጸሎተ ሐሙስ በዓል በመንበረ ጸበዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከበረ
የጸሎተ ሐሙስ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ ትህትና እየታሰበ በተለያዩ ስነ ስርኣቶች ተከብሮ ውሏል፡፡ክርስቶስ በዛሬዋ እለት የሐዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በማጠብ ትህትናን እና ታዛዥነት ማስተማሩን በማሰብ ነው በዓሉ የሚከበረው።በዛሬው ዕለትም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥነ ስርዓቱ ሲከናወን ውሏል፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን እግር፥ […]
ቃለ ዓዋዲው ስለሰንበት ትምህርት ቤት አደረጃጀት ምን ይላል?
መግቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጉብዝናቸው ወራት ፈጣሪያቸውን እንዲያስቡ የተጻፈላቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል የሚያምኑ እና የሚታመኑ ወጣቶች በጉብዝናቸው ወራት ፈጣሪያቸውን ያስቡ ዘንድ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ደረጃ ተጠሪነቱ ለሰበካ ጉባኤው ሆኖ የተደራጀ የወጣቶች የትምህርት፣ የጥናትና ምርምር እና የጸሎት ማዕከል ነው፡፡ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ስለ ቤተክርስቲያን አደረጃጀት እና መዋቅራዊ አሠራር፣ ስለ […]
በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት ምልአተ ጉባኤ ተካሄደ
የካቲት 23 ቀን 2011 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት መካከል የፍቅር አገልግሎት እንዲዳብር ለመወያየት ታስቦ ምልአ ተጉባኤ ተካሂዷል፡፡ ጉባኤው የተጠራበት ዓላማ በተሰጣቸው እውቀት፣ ጊዜና ገንዘብ ውብና ማራኪ የሆነ አገልግሎት እያበረከቱ ያሉ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላትን አንድነት አስጠብቆ የነበረውና ያለውን አገልግሎት አጠናክሮ ለማስቀጠል ነው፡፡ በጉባኤው ከመንበረ ፓትርያርክ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ […]
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ 6ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፬ኛ ፓትርያርክ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ ከ34 በላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የእስልምና ዋና ሐላፊ ሸክ አህመድ፣ የቤተክህነት ሠራቶኞች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በርከት ያሉ ምእመናንና እንግዶች በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ […]
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት ወቅታዊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ወቅታዊ አቋም አወጣ
ሰንበት ትምህርት ቤቱ በመግለጫው አሁን ያለበትን ሁኔታ በዝርዝር ያተተ ሲሆን የካቴድራሉ ጽ/ቤት ከብዙ ምክክር እና ውይይት በኋላ በወሰደው የማስተካከያ እርምጃ በጊዜያዊ አመራር እየተመራ ያለ መሆኑ ተገልጿል። ጊዜያዊ አመራሩም ሆነ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላቱ ይህን አቋም ለምን ማውጣት እንዳስፈለገ ሲገልፁ በተለያዩ ሚዲያዎች እየተናፈሱ ያሉ ወሬወች የሰንበት ትምህርት ቤትቱን ምልአተ ጉባዔ ያላማከለ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቱን ወቅታዊ እና […]
ቅዱስ ሲኖዶስ የዴርሱልጣን ገዳም ጉዳይን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ
በስመአብወወልድወመንፈስቅዱስአሐዱአምላክአሜን! የኢትዮጵያውያን ይዞታ በሆነው በዴርሱልጣን ገዳም የቅዱስ ሚካኤል ቤተመቅደስ እድሳት ላይ የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባላት ያሳዩትን ሕገወጥ ተቃውሞ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፤ ሁላችሁም እንደምታውቁት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኢየሩሳሌም ካሏት ጥንታውያንና ታሪካውያን ቅዱሳት መካናት ውስጥ አንዱና ዋናው በዴርሱልጣን የሚገኘው የመድኀኔዓለም፣ የአርባዕቱ እንስሳ እና የቅዱስ ሚካኤል ገዳማት ናቸው፡፡ ከታሪክ እንደምንረዳው […]
የጥቅምት 2011 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ባለ 15 ነጥቦች መግለጫ በማወጣት ተጠናቀቀ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የመክፈቻው ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ […]