0808

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተለምዶ 22 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በመገንባት ላይ ያለውን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሁለገብ ሕንጻ ጎበኙ!!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተለምዶ 22 ሁለት እየተባለ በሚጠራው አካባቢና ጎላጎል ሕንጻ ጎን እየተገነባ የሚገኘውን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሁለገብ የልማት ሕንጻ አርብ ሰኔ 2 ቀን 2009 ዓ.ም ከቦታው ድረስ ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡የጉብኝቱ መርሐ ግብር በተካሄደበት በዚሁ ዕለት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአዲስ አበባ […]

0035

የገብረ ሰላም በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ!!!

በየዓመቱ በትንሣኤ ዋዜማ ሲከበር የቆየው የገብረ ሰላመ በዓል በዘንድሮው ዓመት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር ጎይቶኦም ያይኑ እና የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት […]

0296

የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር ሥርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ

በኢትዮጵያ አርተዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቀመረ ዲሜጥሮስ አቆጣጠር መሠረት በየዓመቱ ሲከበር የቆየው የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር በዓል በዘንድሮውም ዓመት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ፓትርያርክ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ልብሰ ተክህኖ በለበሱ […]

390

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ 4ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ!!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 4ኛ ዓመት በዓለ ሢመት የካቲት 24 ቀን 2009 ዓ.ም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ባለቤት ወ/ሮ መዓዛ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የመንፈሳውያን ኮሌጆች ተወካዮች፣ የአዲስ […]

ትምህርተ ሃይማኖት ዘቅድስት ሥላሴ

ለክርስትና ሃይማኖት መሠረቱ ማእከሉና መደምደሚያው ምሥጢረ ሥላሴ እንደሆነ ይታወቃል ምክንያቱም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን ነሥቶ ሰው ከሆነ በኋላ የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት የታወቀና የተረዳ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ ይህም በዚህ በልደት እና በጥምቀት ሰሞን በቂ ትምህርት ሊሰጥበት የሚገባ ነው፡፡እግዚአብሔር ወልድ ከቅድስት ድንግል  ማርያም ሰው ሆኖ በሥጋ  ከመወለዱ በፊት […]

2061

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሠራተኞች ልዩ የፅዳታ ዘመቻ አካሄዱ

የካቴድራሉ ልዩ ልዩ ሠራተኞች ጥቅምት 23/2009 ዓ.ም በካቴድራሉ ቅጥር ግቢ በዓይነቱ የተለየ የፅዳታ ዘመቻ በህብረት አካሂደዋል፡፡ይህ አባቢውን/ግቢውን የማጽዳት ሥራ ሲካሄድ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን 1ኛው እና 2ኛው የፅዳታ ዘመቻ ጥቅምት 9 እና 16/2009 ዓ.ም  መካሄዱ ይታወቃል፡፡ይህ ዓይነቱ ገዳማዊ የሥራ ዘመቻ ለቤተ ክርስቲያን አዲስ ባይሆንም  በተለይም በካቴድራሉ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መነኮሳቱ፤ካህናቱ፤ዲያቆናቱ ፤መዘምራኑ እና የአካባቢው ምእመናን በህብረት እንዲህ […]

1846

የሐምሌ ሥላሴ በዓለ ንግሥ በመንበረ ጸባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ!!

በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን የሚከበረው የአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ መለኮታዊ በዓለ ንግሥ በዘንድሮው ዓመት 2008 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡ በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ እንድሪያስ የካቴድራሉ የበላይ ኃላፊ በቅዱስነታቸው መልካም ፈቃድ እለቱን አስመልክተው ሰፋ […]

pp002

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የ2008 ዓ.ም የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለበርካታ ችግረኞች ታላቅ የምሳ ግብዣ አደረገላቸው!!

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እሑድ ሚያዚያ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ቁጥራቸው ከ1,000 በላይ ለሚሆኑ ነዳያን /ችግረኞች  ሰፊ የሆነ የምሳ ግብዣ ያደረገላቸው መሆኑን የዝግጅት ክፍላችን ከቦታው ድረስ በመሄድ አረጋግጧል፡፡ ይህ ታላቅ የምሳ ግብዣ የተከናወነበት ቦታ ቀደም ሲል በነገሥታቱ፣ በመሳፍንቱ፣ በመኳንንቱና በደጅአዝማቾቹ ዘመን በተመሠረተውና 107 ዓመት እድሜ ባስቆጠረው የካቴድራሉ የሰንበቴ […]

0478

የግብረ ሰላም በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጰሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፤የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅና የክፍል ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ቅዳሜ ሚያዝያ 22 ቀን 2008 ዓ.ም የግብረ ሰላም በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ ለዘተንስአ […]

0444

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተገኝተው የጸሎተ ሐሙስን በዓል አከበሩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ተክለሃይማኖት ሐሙስ ሚያዝያ 20 ቀን 2008 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመገኘት በካቴድራሉ ለተገኘው በርካታ ምዕመናን አባታዊ ትምህርት እና ቃለ ምዕዳን አስተላልፈዋል፡፡ በአስተላለፉት አባታዊ ትምህርት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ሥርዓተ […]

አስተያየትዎን ይጻፉልን