017

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ጾመ ፍልሰታን አስመልክተው ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን

                  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን  በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ  ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ  የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችኹ   በሕማም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችኹ  የሕግ ታራሚዎች ኾናችኁ በማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤ የተወደዳችኹ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ የቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጆች ምእመናንና ምእመናት […]

0025

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ አረጋወያን ለ10ኛ ጊዜ እረዳታ ተሰጠ

                 በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ (Bsc) “ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው እግዚአብሔር ከክፉ ያድነዋል፡፡” መዝ. 40÷1 “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ”2ኛ ቆሮ. 9÷7 ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በድህረ ገፃችን አማካኝነት ወጣት ብሩክ አስራት የክርስትና ስሙ ግርማ ጽዮን ከዛሬ 10 ወራት በፊት ጀምሮ ለካቴድራሉ አረጋውያን የሚሆን በየወሩ ለአረጋውያኑ የሚያስፈልጋቸውን የምግብ እርዳታ እያደረገላቸው መሆኑን ስንዘግብ መቆየታችን […]

0013

አዲሱ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

                             በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ (Bsc) በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ና በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ አማካኝነት ከሐምሌ 26 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. ጀምሮ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት ክቡር ሊቀ ስልጣናት አባ ኪሮስ ፀጋዬ ሲሆኑ እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2ዐዐ5 […]

0003

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለሥራ ኃላፊዎች የ3 ቀን የምክክርና የግንዛቤ ማስጨባጫ ሥልጠና ተሰጠ

                 “ክፉውን ነገር ተጸየፉት ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ”ሮሜ 12÷9

0003

መልካም አስተዳደር ለዘላቂና ሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን እድገት በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሥልጠና የተጀመረው ሐምሌ 9/2005 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ሥልጠናው እየተካሄደው ያለውም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንገል አዳራሽ ነው፡፡ በዚሁ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ሥልጠና ተካፋይ የሆኑ ሥራ ኃላፊዎች፡-

1. የሀገረ ሰብከት ሠራተኞች፣

2. የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ፀሐፊዎች፣

3. የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርት፣

4. የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የክፍል ኃላፊች፣

5. የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች ናቸው፡፡

ሥልጠናውን በፀሎት የከፈቱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሲሆኑ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአ/አ/ሀ/ስ/የቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀጳጳስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣መጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣንት በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ተገኝተዋል፡፡

የሥልጠናውን መርሃ ግብር የሚመሩት መጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ ሲሆኑ ከፀሎቱ መርሃ ግብር በኃላ በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአ/አ/ሀ/ስ/የቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀጳጳስ አማካኝት ስለ ሥልጠናው አስፈላጊነት በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመቀጠልም ከመንግስት ተወካይ አጠር ያለ ፀሑፍ ተነቧል፡፡ከዚህ በኋላ ወደ ሥልጠናው የተገባ ሲሆን ሥልጠናው ከፍተኛ ሞያ ባካበቱ በመንግስትና በግል የሚሠሩ ባለሞያዎች ሙሉ ሥልጠናው ተካሂዷል፡፡ተሰብሳቢዎችም ከፍተኛ የሆነ ተሳትፎ አድርገዋል ፡፡

ሥልጠናው በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት እና በአድባራትና ገዳማት የሚገኙ መሪዎችንና አገልጋዮችን የመሪነትና የሥራ ብቃት ደረጃ ከፍ ለማድረግ ለታሰበው የአሠራር ለውጥ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የታቀደ ሥልጠና ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ስለ ሥልጠናው ዓላማ አስመልክቶ ሲናገሩ፣ ሀ/ስብከቱ በአስተዳደር፣ በፍትሕ መንፈሳዊ፣ በማኅበራዊ አገልግሎትና በምጣኔ ሀብት በኩል በሕግና ሥርዐት በመመላለስና በመደራጀት ውጤታማ ሥራ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡ በርካታ ዕቅዶቹን ተግባራዊ ለማድረግ በሀ/ስብከቱ የሚገኙ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች በለውጡ አጀንዳዎች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በዘርፉ የላቀ ክህሎትና ዕውቀት ባላቸው ባለሞያዎች የሥልጠናና ምክክር መርሐ ግብሩን ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡

ከሀ/ስብከቱ የሥራ ግዝፈትና ካለው ሰፊ የፋይናንስ ፍሰት አንጻር ሲመዘን ችግሩ የተጋነነና የገዘፈ እንዳልኾነ የሚያምኑት ብፁዕነታቸው፣ ተጠቃሽ ጉድለቶችን ሲዘረዝሩ፡-

1. የመልካም አስተዳደር ግድፈትና ማሽቆልቆል፣

2. ዘመኑን የዋጀ የምጣኔ ሀብት አስተዳደርና ዘመናዊ የሒሳብ አሠራር ክፍተት፣

3. የእርስ በርስ አለመናበብና የጎጠኝነት ስሜት፣

4. ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዐት አለመዘርጋት

5. የተአምኖ ግብርና እና የሥነ ምግባር ደረጃ ዝቅ ብሎ መገኘትና የመሳሰሉትን እንደኾኑ ጠቁመዋል፡፡ ብፁዕነታቸው እንዳብራሩት፣ መልካም አስተዳደር÷ ከእግዚአብሔር በተሰጠን ሥልጣንና ሓላፊነት የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት በሁሉም መስክ በጎ አርኣያነት ያለው መልካም እረኛ መኾን ማለት ነው፡፡ በመልካም አስተዳደር መርሕ መሠረት ‹‹ሓላፊ ነኝ፤ አዛዥ ነኝ›› ከሚል መኮፈስ ይልቅ የአገልጋይነትና የመሪነት ስሜት መላበስ ተገቢ ነው፡፡ ‹‹የምንመራትና የምናገለግላት ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር በደሙ የዋጃት እንደመኾኗ መጠን የተቀበልነው አደራ እጅግ ታላቅና በልዑል እግዚአብሔር ፊት ቀርበን ዋናውን ከትርፍ ጋራ የምንጠየቅበት ነው፤›› ያሉት ረዳት ሊቀ ጳጳሱ፣ የምንመራቸው ሰዎችና የምናስተዳድረው ሀብት የእግዚአብሔር ሀብት ነውና ሓላፊነታችን እጅግ ከባድ እንደኾነና አገልግሎታችንም በዚሁ አቅዋምና መንፈስ ሊቃኝ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ ሐምሌ 9/2005 በተጀመረውና በ11/2005 የሚጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የሥልጠና መርሃ ግብር፡-

1. መልካም አስተዳደር እና ጠቀሜታው

2. የግዥ ሥርዐት፣ ተያያዥ ችግሮቹና የመፍትሔ አቅጣጫ

3. ዘመናዊ የፋይናንስ አሠራር፣ አያያዝና ተጠያቂነት

4. የዕቅድ፣ ቁጥጥር፣ ክትትል እና ግምገማ ሥርዐት

5. ውጤታማ መሪነት ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት

6. ሙስናና ተያያዥ ችግሮች

7. የግጭት መንሥኤ እና አፈታት የሚሉ ርእሰ ጉዳዮች የተካተቱ ሲኾን የዘርፉ ባለሞያዎችና ምሁራን ከቤተ ክርስቲያናችን ተጨባጭ ችግሮች ጋራ በማዛመድ በሚያቀርቧቸው መነሻዎች ተሳታፊዎቹ ውይይት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡ የአሁኑን ጨምሮ በሁለት ዙሮች ከሚካሄደው የሥልጠናና ምክክር ጉባኤ ጋራ በተያያዘ በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት እና በአዲስ መልክ በተሠራው መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት በሚቋቋሙት የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የሓላፊዎችና ሠራተኞች ምደባ የካሄዳል፡፡

ሀገረ ስብከቱ ቃል በገባው መሠረት ከሐምሌ 17/2005 በአዲሱ መዋቅር መሠረት ሙሉ ሥራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአዲሱ አደረጃጀት ሀ/ስብከቱ ለመልካም አስተዳደር በሚያመቹ ሰባት የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ሲኾን በቋሚ ሲኖዶሱ ተሻሽሎ በጸደቀለት ልዩ መተዳደርያ ደንብ መሠረት በአግባቡና በሥርዓቱ ሥራውን መሥራት ያስችላል ይህ ልዩ ጊዚያዊ መተዳደርያ ደንብ እስከ ጥቅምት ወር ፳፻፮ ዓ.ም ብቻ በጊዜያዊነት የሚያገለግል ሲሆን የሥራ ምደባውም በትምህርት ዝግጅትና በአገልግሎት ዘመን እንደ ሆነ ለማውቅ ተችሏል፡፡ ይህን በተመለከተ ሀገረ ስብከቱ ሥራንና ሠራተኛን ለማገናኘት ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ በማስቀመጥ ሓላፊነትና ተጠያቂነት ያለው የአሠራር ሂደት በቁርጠኝነት እንደሚከተል የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የሥልጠናው መርሐ ግብር ዓላማ ባብራሩበት ወቅት አስረድተዋል፡፡

የኮርሱን ጽሑፍ ዳውንሎድ ያድርጉ (ውጤታማ መሪነት)

የኮርሱን ጽሑፍ ዳውንሎድ ያድርጉ (ሙስና)

{flike}{plusone}

የብፁዕነታቸውን ሙሉ ንግግር ከዚህ ቀጥሉ እንደሚከተለው ይቀርባል

5.5

ዓመታዊው የዓጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በዓል በድምቀት ተከበረ

በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚከበረው ዓመታዊው የሥላሴ በዓል በዚህ ዓመትም በመንበረ ጸባዖት ቅድሰት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኩሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ሁኔታ በዓሉ ተከብሮ ውልዋል፡፡ በዚሁ ዕለት አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በአብርሃም ቤት […]

md1

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት ኃላፊዎች ከብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአ/አ/ሀ/ስ/የቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀጳጳስና ከአ/አ/ሀ/ስ/ዋና ስራ አስከያጅ ጋራ የትውውቅ መርሃ ግብር ተካሄደ

                    በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ ሰኔ 14/2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 2.30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ የትውውቅ መርሃ ግብሩ የተካሄደ ሲሆን በዚሁ ዕለት አዲሱ አስከያጅ መጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በአ/አ/ሀ/ስ/የቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀጳጳስ አማካኝነት /ጋባዥነት ራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ በተፈቀደላቸው መሠረት በአጭሩ ከጀመሪያ ጀምሮ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አሰከያጅነት እሰከ ተሶሙበት የነበረውን […]

0037

በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለሚጦሩ አረጋወያን ለ9ኛ ጊዜ እረዳታ ተሰጠ

“ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው እግዚአብሔር ከክፉ ያድነዋል፡፡” መዝ. 40÷1 “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ”2ኛ ቆሮ. 9÷7 ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በድህረ ገፃችን አማካኝነት ወጣት ብሩክ አስራት የክርስትና ስሙ ግርማ ጽዮን ከዛሬ 9 ወር በፊት ጀምሮ ለካቴድራሉ አረጋውያን የሚሆን በየወሩ ለአረጋውያኑ የሚያስፈልጋቸውን የምግብ እርዳታ እያደረገላቸው መሆኑን ስንዘግብ መቆየታችን የሚታወስ ሲሆን አሁንም እንደተለመደው ለ9ኛ […]

00001

የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ተጠናቀቀ

ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 30/ 2005 ዓ.ም. ድረስ ሲካሔድ የሰነበተው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያኗ አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ውሳኔዎች በማሳለፍ ተጠናቀቀ፡፡             በዚህም መሠረት የሚከተሉትን ጠቅለል ያሉ ውሣኔዎች ተላልፈዋል፡፡  የቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 […]

0001

በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት የውሃ ማጣሪያ ማሽን ተገጥሞ ሥራ ላይ ዋለ

የውሃ ማጣሪያ ማሽኑ እስፕላሽ ኢንተርናሽናል ከሚባል ግብረ ሰናይ ድርጅት በእርዳታ የተገኘ ሲሆን ለዚሁ ሥራ ከ120,000.00 ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሚሊዮን ገልጸዋል፡፡ ማሽኑ የተለያዩ ጀርሞችና ቆሻሻን በሚገባ ከመከላከሉም በላይ የምንጠጣው ውሃ ጥሩ ጣዕም እንዲኖረው እንደሚያደርግም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ በዚሁ የምረቃ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ክቡር ሊቀ ሥልጣናት አባ ገ/ሥላሴ የካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸው ባስተላለፉት […]

001

በዓላትን ማክበር ያለብን ያጡትንና የተቸገሩትን በማሰብ/በመርዳት መሆን እንዳለበት ተገለፀ

001

የትንሣኤን በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሞትን በመስቀል ላይ ከተቀበለ በኋላ በሦስተኛው ቀን መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ከሙታን ተለይቶ የተነሣበት ዕለት ነው፡፡

የትንሣኤውም ዓላማ የሰው ልጅ በመቃብር ፈርሶ በስብሶ አለመቅረቱን ለማስረዳት፣ ክርስቲያኖች ከሞት በኋላ ተስፋ ትንሣኤ እንዳለን ለማጠየቅና ከወደቅንበት ኃጢአት በንስሐ መነሣት እንዳለብን ለማስተማር መሆኑን መገንዘብ ይገባናል፡፡

በቤተክርስቲያናችንም እነዚህ ታላላቅ ዓላማዎች ያሉት የትንሣኤ በዓል በደመቀ ሁኔታ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም ጠላቶቻችን ሞትና ሰይጣን ድል የተነሡበት፣ የሰው ልጅም ከሰይጣን ባርነት ነጻ የወጣበት፣ በአዳምና በሔዋን ምክንያት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ የፈረሰበት፣ የድል፣ የነጻነትና የሰላም ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህም በቤተክርስቲያናችን የትንሣኤ ሰላምታ የተለየ ነው፡፡ ይኸውም፡-

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን. . . በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን. . . አጋዐዞ ለአዳም ሰላም . . . እም ይእዜሰ ኮነ . . . ፍስሐ ወሰላም የሚል ነው፡፡

እንግዲህ ይህንን በዓል በየዓመቱ ስናከብር ዓላማውን ዘንግተን በዓሉን የምግብና የመጠጥ ብቻ እንዳናደርገው መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በልዩ ልዩ መንገድ በፈቃዱ የሰይጣን ባሪያ የሆነ፣ ከክርስቲያናዊ ምግባርና ትሩፋት የራቀ ሁሉ ራሱን እንዲመረምርና ለመልካም ሥራ እንዲነሣ የሚያደርግ በዓል መሆኑን ተረድተን ራሳችንን ልናስተካክል ያስፈልጋል፡፡ በዓለም በሥጋ ሥራ በመመላለስ የምንኖር ከዚህ ሥራችን በልቦና ትንሣኤ ተነሥተን የንስሐ ፍሬ የምናፈራበት እንዲሆን ልንተጋ ይገባናል፡፡ ክርስትናችን በስም ብቻ ተወስኖ በዓለም በሥጋ ሥራ የምንኖር ደግሞ ራሳችንን በመመርመር በንስሐ ታጥበንና ታጥነን ትንሣኤውን ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን በመቀበል እናክብረው፡፡

ሁልጊዜም በዓሉን ከነዳያን ጋር እየተካፈልን የምንኖር መልካም ልማድ ያለን የትሩፋት ሥራችንን እያሳደግን፣ በሃይማኖትና በምግባርም እየበረታን ልንሔድ ያስፈልጋል፡፡ ክርስትና ሠላሳ፣ ስድሳና መቶ ፍሬ የምናፈራበት የዕድገት ጉዞ እንጂ በምንሠራት ጥቂት የትሩፋት ሥራ ብቻ ረሥተን የምንቆምበት አይደለምና በትሩፋት ላይ ትሩፋት፣ በጸጋ ላይ ጸጋ እየጨመርን መሔድ ይገባናል፡፡

{flike}{plusone}

አስተያየትዎን ይጻፉልን